ስለ ጽ/ቤቱ

AAHAPCO Bldg.

ኤች.አይ.ቪ / ኤድስ በከተማችን እያስከተለ ካለዉ ችግር አንፃር በከተማችን ውስጥ ለሚገኙ ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቋቋሙ ድርጅቶንች እና ማህበራትን በማስተባበርና ከፍተኛ ድጋፍ ለመስጠት እንዲቻል የተለየ የመንግስት መ/ቤት እንዲቋቋም በማስፈለጉ የአዲስ አበባ ኤችአይቪ/ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ወረርሽኝን በተጠናከረ መንገድ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በጥር 1993 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡

 


ራእይ

አዲስ አበባ ከኤች.አይ.ቪ ወረርሽኝ ስጋት ነፃ ሆና እና ኤችአይቪ/ኤድስ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ ተወግዶ ማየት፣


ተልእኮ

መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የእምነት ተቋማት እና በማህበረሰብ ላይ የተመሰረቱ አደረጃጀቶች የፀረ-ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ እንቅስቃሴዎችን በማስተባበር እና አቅማቸውንም በማጐልበት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የተቀናጀ እና ውጤታማ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር አገልግሎቶች እንዲሰጡ ማድረግ፣


ግብ

በአሁኑ ወቅት ያለውን የኤች.አይ.ቪ የመያዝ ክስተት ከ1.4 በመቶ እ.ኤ.እ. በ2ዐ11 ወደ ዐ.4 በመቶ እንዲቀንስ ማድረግ፡፡

እ.ኤ.አ. በ2ዐ11 ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ በግለሰቦች፣ በቤተሰቦች፣ በማህበረሰቦች እና በሕብረተሰቡ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በመቀነስ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው ውሰጥ የሚገኙ ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸው 1ዐዐ በመቶ እንክብካቤ እና ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል የሕክምና ተደራሽነትን በአግባቡ ማስፋፋት፡፡


አላማዎች

በአዲስ አበባ ከተማ አላማዎቻችንን የሚከተሉት ናቸው፡-

በከተማችን በኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳታፊ ለሆኑ ድርጅቶች በቴክኒክ፣ በገንዘብ እና በሌሎች ድጋፎች አማካኝነት አቅማቸውን ማሳደግ፣

በኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ዙሪያ በመስራት ላይ ባሉ ድርጅቶች እንዲሁም በዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑትን በማስተባበር የአደረጃጀት ትስስር መፍጠር፣

ልዩ ልዩ የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር እንቅስቃሴዎችን ውጤታማነት መከታተል እና መገምገም፣

የኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ ጥበቃ እና ቁጥጥር እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ሃብቶችን ማንቀሳቀስ፣

ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝና እና በዚህ ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች ድጋፍ እና እንክብካቤ ለማድረግ ከተግባሪ ወገኖች ጋር በትብብር መስራት፣

ሴቶች፣ ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች እና ወጣቶች የመሳሰሉ ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑትን ለመደገፍ ከተግባሪ አጋሮች ጋር በትብብር መስራት፣

የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር እንቅስቃሴዎችን መደገፍ እና ማበረታታት፣