መግቢያ

Addis Ababa City Hall

ኢትዮጵያ ኤች ኤ ቪ/ኤድስ ከፍ ባለ የስርጭት መጠን ከሚገኝባቸዉ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሃገራት የምትመደብ ሃገር ናት፡፡ እ.ኤ.አ በ 2006 ይፋ በሆነው በስድስተኛው ኤድስ በኢትዮጵያ ሪፖርትና በስነ-ህዝብ ጤና ዳሰሳ ጥናት ጥምር ስሌት (Single Point Estimate) መነሻነት በቀረበው ግምት መሰረት የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ የስርጭት መጠን 2.4% ሲሆን 1,216,9ዐ8 የሚሆኑ ወገኖች በ2010 እ.ኤ.አ ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ በአማካይ በከተማ የሚታየው የስርጭት መጠን 7.7% ሲሆን፣ ይህም በገጠር ከሚታየው የዐ.9% አማካይ የስርጭት መጠን በ8 እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት ምንጮች መገንዘብ እንደሚቻለዉ በአዲስ አበባ ከተማ በ2ዐ1ዐእ.ኤ.አ. በአዲስ አበባ 21ዐ,3ዐ6 የሚሆኑ ወገኖች ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ የሚገመት ሲሆን በከተማ ያለው የኤችአይቪ/ኤድስ የስርጭት መጠን ደግሞ 9.2% ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እ.ኤ.አ. በ2ዐዐ9 22,214 ሰዎች በኤች.አይ.ቪ የተያዙ ሲሆን፣ በዚሁ አመት 5948 ሰዎች በበሽታው ምክንያት ሕይወታቸውን እንዳጡ ይገመታል፡፡

ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ ከሚገመቱት የከተማዋ ነዋሪዎች መካከልም 7ዐ,ዐ97 የሚሆኑት የፀረ-ኤድስ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው እንደሆኑ ይገመታል፡፡


 

በቅርቡ የተከናወኑ ተግባራት

የኤች አይ ቪ የምክክርና ምርመራ አገልግሎት አከባበር ቀን አስመልክቶ የተከናወኑ ተግባራት

New Office Bldg.“ጤናማ እናት” በሚል ርዕስ 600 እርጉዝ እናቶችና ባሎቻቸው 800 የማህበረሰብ ተቋማቶች በጠቅላላው 1500 ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ስብሰባ ማዕከል የግማሽ ቀን የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በዕለቱ ከጤና ቢሮ በሚመለከተው ባለሙያ ከእናት ወደ ልጅ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ ትምህርት ቀርቧል::

ተጨማሪ ለማንበብ...>>

የኤች አይ ቪ የምክክርና ምርመራ አገልግሎት አከባበር ቀን አስመልክቶ የተከናወኑ ተግባራት

New Office Bldg. ለአካል ጉዳተኞች የምክርና ምርመራ አገልግሎት ለመሰጠት በታቀደው መሰረት መስማት የተሳናቸው የህብረተሰባችን ክፍሎች በምልክት ቋንቋ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከዘውዲቱና ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር አገልግሎቱ መሰጠት ተጀመረ፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ...>>

የአ/አ/ኤ/ኤ/መ/መ/ጽ/ቤት የቢሮ ለውጥ አደረገ

New Office Bldg.የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ቀድሞ ከነበረበት ጽ/ቤቱ ወደ ካዛንቺስ አካባቢ ወደሚገኘው ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሲጠቀምበት ወደነበረው ህንጻ በከፊል የተዛወረ ሲሆን አምባሳደር ቲያትር አካባቢ የሚገኘውን ቢሮውን የጽ/ቤቱ ኤድስ መረጃ ማዕከል በማድረግ እያደራጀ ይገኛል፡፡ አዲሱ ቢሮ ካዛንቺስ ከመናኽሪያ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው መንገድ ወደ ውስጥ 150 ገደማ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

የቢሮውን ፎቶ ና ቦታ ጠቋሚ ካርታ ለማየት እዚህ ይጫኑ...>>

የምክክርና ምርመራ አገልግሎት ቀን “መመርመራችን ለቤተሰባችን ” በሚል መሪ ቃል በፖሊስ ማርሽ ባንድና በሰርከስ ትዕይንት ለሶስት ቀናት በከተማዋ በመኪና ባንዶችን እንዲቀሰቅሱ በማድረግ ቅስቀሳ ተደረገ፡፡

በአራት ቦታዎች ከእናት ወደ ልጅ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ የሚያሳይ መልዕክት የያዙ ቢል ቦርድ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር በሚበዛባቸው ቦታዎች እንዲተከሉ ተደረጉ፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ...>>

ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በመከላከል ዙሪያ የቲቪ ውይይት ተደረገ

ከእናት ወደ ልጅ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ የምክክርና ምርመራ አገልግሎ እንዲሁም ሌሎች የጤና እና የኤች አይ ቪ /ኤድስ አገልግሎቶች አሁን ያሉበት የአፈጻጸም ሁኔታ ያጋጠሙ ችግሮች ምርጥ ተሞክሮዎች የተጠቃሚዎች ምስክሮች፣ ለወደፊቱ መደረግ የሚገባቸውን የመፍትሄ ሀሳቦችና አቅጣጫዎች በቴሌቪዥን ሁለት (ኢቴቪ 2) የፓናል ውይይት ከ70 በላይ የሚመለከታቸው አጋር ድርጅቶች በተገኙበት ቀረጻ በማድረግ ሁለት ጊዜ በቴሎቪዥን በፕሮግራም መልክ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡

የምክክርና ምርመራን ቀን በማስመልከት በተንቀሳቃሽ ስልክ አጭር መልዕክት ተላለፈ

የምክክርና ምርመራ አገልግሎት ቀን አከባበር “መመርመራችን ለቤተሰባችን ” በሚል መሪ ቃል በሞባይል መልዕክት ለ 1,000,000 ያህል ሰዎች በቀጥታ ተሰራጭቷል፡፡

በምክክርና ምርመራ አገልግሎት የተሰማሩ በጤና ተቋማት የሚገኙ ካውንስለሮች ኬዝ ኮንፈረንስ ለሶስት ቀናት የአቻ ለአቻ የልምድ ልውውጥና ኬዝ የተመረጠ ጠቃሚ የሆነ ርዕስ ላይ ትምህርታዊ ጥያቄና መልስ የተካሄደ ሲሆን በአገልግሎቱ ያጋጠማቸው ችግሮች በካውንሰለሮች ቀርቦ መልስ ተሰጥቶበታል፡፡

በወጣቶች የክረምት ንቅናቄ ላይ ብዙ ወጣቶች በፈቃደኝነት የኤች አይ ቪ ምርመራ አደረጉ

በከተማው የክረምት የወጣቶች ዘመቻ ላይ የኤች አይ ቪ/ኤድስ የመከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራሞ ከ20,000 በላይ ወጣቶች ንቅናቄ የተፈጠረ ሲሆን የምክክርና ምርመራ አገልግሎቶች ወጣቱ እንዲመረመሩ በተደረገው ጥረት መሰረት ብዙ ወጣቶች ምርመራ አድርገዋል፡፡

የአባላዘር በሽታን ለመከላከልና ለማከም የሚያስችሉ ክሊኒኮች ተከፈቱ

የአባላዘር በሽታዎችና ኤች አይ ቪ/ኤድስ በሚል ፕሮጀክት በይበልጥ የተጋለጡ ሴተኛ አዳሪዎች ከቤተሰብ መምሪና ከሶስት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሚስጠራዊነታቸው የተረጋገጠ ልዩ የሆኑ የህክምና ክሊኒኮች ተከፈቱ፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ...>>