ድጋፍ እና እንክብካቤ
ወላጆቻቸውን ያጡና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ሕፃናት
ወላጆቻቸውን ያጡና እና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ሕፃናት ጥምር ማህበራዊ፣ ስነልቦናዊ፣ የምግብ፣ የጤና እንዲሁም ሌሎች በርካታ ችግሮች አሉባቸው፡፡ በበርካታዎቹ ሁኔታዎች እነዚህ ሕፃናት ሌሎች ብዙ ተጨማሪ ልጆችን በሚያሳድጉ ቤተሰቦች ውስጥ በድህነት የኢኮኖሚ ሁኔታ ወይም እጅግ አነስተኛ የገቢ መጠን ካላቸው ከአያቶቻቸው ጋር ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች ሕይወታቸውን በራሳቸውን ለመምራት በሚያደርጉት ጥረት በታላላቅ ልጆች ምሪት ስር ናቸው፡፡
ስለሆነም የተቀናጀ የት/ቤት፣ የምግብ፣ የስነልቦና እና የፋይናንስ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት ረገድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በማስተባበር በልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንሰራለን፡፡ እነዚህም ድጋፎች የሚሰጡት ሕፃናቱ በቁጥር ከ14 በላይ ከሆኑ ነው፡፡ በሌላ በኩል ብዛታቸው ከ14 በታች ከሆነ እንዲህ ያለውን የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴ ድጋፍ ለሕፃናት የማሳደጊያ አገልግሎት ለሚሰጡ ሰዎች እንሰጣለን፡፡
የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኙ ሰዎች፡-
ጽ/ቤታችን ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝ ሰዎች የምግብ፣ የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴ እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ተግባራትን ያደርጋል፡፡ ይህም የሚከናወነው በግል እንዲሁም እነዚህ ሰዎች በተደራጁባቸው ማህበራት አማካኝነት ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ማህበራት ቅንጅት ወይም ትስስር አለ፡፡ ይህ ትስስር ጽ/ቤትታችን ጋር በቅርበት ተባብሮ በመስራት ለተጠቃሚዎች የተጠናከረ ድጋፍ ይሰጣል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከኤች.አይ.ቪ ጋር ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች በጠቅላላው በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስራ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የማጠናከር ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
በቤት ለቤት የሚሰጥ እንክብካቤ
ይህ የማህበረሰብ የበጐ ፈቃደኝነት የስራ እንቅስቃሴ ነው፡፡ አላማውም ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች፣ ለወላጆቻቸውን ላጡና ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች እንክብካቤ እና ድጋፍ መስጠት ነው፡፡ የፀረ-ኤድስ ነፃ ሕክምና በአለም አቀፍ ደረጃ ወይም ለሁሉም ተደራሽ መሆን ከጀመረ በኋላ የቤት ውስጥ እንክብካቤ የሚሰጣቸው የአልጋ ቁራኛ ታማሚዎች ቁጥር ቀንሷል፡፡ በዚህም ምክንያት በቤት ውስጥ እንክብካቤ የሚሰጡ ሰዎች በአሁኑ ወቅት የመድሃኒት አወሳሰድ፣ የስነ-ልቦና ድጋፍ ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች፣ ለወላጆቻቸውን ላጡና ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ልጆች በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም ሌላ የሳንባ በሽታ ታማሚዎች ናቸው ተብለው ለተጠረጠሩ ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት እንዲላኩ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ፡፡













