የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎች

የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎች እርምጃዎች የተወሰዱት ከኤችአይቪ ቫይረስ ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎች በኢኮኖሚ ረገድ ራሳቸውን እንዲደግፉ እና ከሚያጋጥሟቸው በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎች አንፃር የማህበራዊ ዋስትና እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ እንቅስቃሴ በልማት እና በሰብአዊ እርዳታ ጥረቶች ረገድ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የኤች.አይ.ቪ /ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ይህንን እንቅስቃሴ ለመደገፍ እና ያለውንም ድጋፍ ለመግለፅ ይህንን ስራ በመምራት የተደራጀ አሰራር እንዲኖር ለማድረግ ተንቀሳቅሷል፡፡ በገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎች ጥላ ስር 1ዐሩም ክፍለ ከተማዎች ተሳታፊዎች ለመሆን የቻሉ ሲሆን፣ አዲስ አበባ ከተማ 2ዐ ተግባሪ ድርጅቶች ተሳታፊ ናቸው፡፡ የ2ዐዐ7/2ዐዐ8 ቀጥተኛ የአለም አቀፍ ፈንድ ተጠቃሚዎች በአዲስ አበባ ዙሪያ 1338 ነበሩ፡፡

የአዲስ አበባ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ሁሉንም ድርጅቶች ማለትም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑትን በቴክኒክ፣ በገንዘብ፣ በፕሮጀክት ግምገማ፣ በክትትል እና በግምገማ አማካኝነት ድጋፍ የመስጠት ተግባር ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ይህንን ግብ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት የሚሰራ ሲሆን፣ በገቢ ማስገኛ የሥራ እንቅስቃሴዎች፣ በግብይት እና በገበያ ምርምር ረገድ ከኤች/አይ/ቪ ጋር አብረው ለሚኖሩ ሰዎች እና ለወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናትማህበራት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡


ክፍለ ከተማ

ተግባሪ አጋር ድርጅት

ተጠቃሚዎች

ጠቅላላ

ወንድ

ሴት

አዲስ ከተማ

ቻድ-ኢት

17

53

70

አማኑኤል የሕፃናት መርጃ ድርጅት

19

50

69

አቃቂ ቃሊቲ

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን

22

46

68

የሴቶች ጉዳይ

የለም

36

36

አራዳ

አበበች ጎበና

20

32

52

አይኤስኤፒኤስኦ

4

52

56

ቦሌ

ዳውን ኦፍ ሆፕ

28

50

78

ብራይት ሆፕ ኦርጋናይዜሽን

6

48

54

ጉለሌ

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን

22

61

83

ኤስደብሊውኤኤኢ

7

52

59

ቂርቆስ

ኤፍሲአይዲኤፍ

11

59

70

ኤፍኤስፒኤኦ

14

67

81

ኮልፌ ቀራንዮ

ቲኤስዲኤ

22

48

70

ኤችኤፒኤስሲኦ

15

56

71

ልደታ

ሪስክ ዘ ቻይልድ ኤንድ ዩዝ

23

43

66

ፕሮ-ፖር

10

59

69

ንፋስ ስልክ ላፍቶ

ኤኤአርዲአር

30

46

76

ዳውን ኦፍ ሆፕ

15

57

72

የካ

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን

21

35

56

ዳውን ኦፍ ሆፕ

12

44

56

ኦፒአርኤኤ

የለም

26

26

ድምር

17 አይፒኤስ በ 10 ክፍለ ከተሞች

318

1020

1338