በቅርቡ የተከናወኑ ተግባራት

 

የአ/አ/ኤ/ኤ/መ/መ/ጽ/ቤት የቢሮ ለውጥ አደረገ

New Office Bldg.

Office Site Location Map

.

 

የኤች አይ ቪ የምክክርና ምርመራ አገልግሎት አከባበር ቀን አስመልክቶ የተከናወኑ ተግባራት

“ጤናማ እናት” በሚል ርዕስ 600 እርጉዝ እናቶችና ባሎቻቸው 800 የማህበረሰብ ተቋማቶች በጠቅላላው 1500 ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ስብሰባ ማዕከል የግማሽ ቀን የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በዕለቱ ከጤና ቢሮ በሚመለከተው ባለሙያ ከእናት ወደ ልጅ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ ትምህርት ቀርቧል:: በሁለት ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝባቸው እናቶች ከወለዱት ከቫይረሱ ነጻ የሆኑ ልጆች ጋር የምስክርነትና ከጥንቃቄ ጉድለት ከቫይረሱ ጋር የተወለደ 9ኛ ክፍል ተማሪ ልጅ እንዲሁም ምስክርነት ቃል የተሰጠ ሲሆን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን / በቴሌቪዥን፣ በተለያዩ ኤፍ ኤም ሬድዮኖችና የህትመት ወጤቶች ተሰራጭቷል፡፡

.

.

የኤች አይ ቪ የምክክርና ምርመራ አገልግሎት አከባበር ቀን አስመልክቶ የተከናወኑ ተግባራት

ለአካል ጉዳተኞች የምክርና ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት መስማት የተሳናቸው በምልክት ቋንቋ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ከዘውዲቱና ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር ለመስጠት ባለሙያዎችን በማሰልጠን ከ 70 በላይ የሚመለከታቸው የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች በተገኙበት በምልክት ቋንቋ በይፋ አገልግሎቱ እንዲጀመር ተደርጓል፡፡

የፖሊስ ማርሽ ባንድ በተለያዩ የከተማዋ ክፍል በመዘዋወር ነዋሪው እንዲመረመር ቅስቀሳ አደረገ

የምክክርና ምርመራ አገልግሎ ቀን “መመርመራችን ለቤተሰባችን ” በሚል መሪ ቃል በፖሊስ ማርሽ ባንድና በሰርከስ ትዕይንት ለሶስት ቀናት በከተማዋ በመኪና ባንዶችን እንዲቀሰቅሱ በማድረግ ቅስቀሳ ተደረገ፡፡ በአራት ቦታዎች ከእናት ወደ ልጅ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ የሚያሳይ መልዕክት የያዙ ቢል ቦርድ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር በሚበዛባቸው ቦታዎች እንዲተከሉ የተደረጉ ሲሆን በዕለቱ የእግር ጉዞ ከ700 በላይ እናቶችና አጋር ድርጅቶች በተገኙበት ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እስከ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ድረስ ጉዞ የተደረገ ሲሆን በሆስፒታሉ ዳይሬክተር ስለ እናቶች ህክምና አገልግሎት ማብራሪያ አድርገዋል፡፡ ሌላው በዕለቱ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢው ውስጥ የቆሙ ቢል ቦርድ ተመርቀዋል፡፡ በተጨማሪም ዕለቱን አስመልክቶ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ክንውኑን ለሕዝብ እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡

 

ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በመከላከል ዙሪያ የቲቪ ውይይት ተደረገ

ከእናት ወደ ልጅ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ የምክክርና ምርመራ አገልግሎ እንዲሁም ሌሎች የጤና እና የኤች አይ ቪ /ኤድስ አገልግሎቶች አሁን ያሉበት የአፈጻጸም ሁኔታ ያጋጠሙ ችግሮች ምርጥ ተሞክሮዎች የተጠቃሚዎች ምስክሮች፣ ለወደፊቱ መደረግ የሚገባቸውን የመፍትሄ ሀሳቦችና አቅጣጫዎች በቴሌቪዥን ሁለት (ኢቴቪ 2) የፓናል ውይይት ከ70 በላይ የሚመለከታቸው አጋር ድርጅቶች በተገኙበት ቀረጻ በማድረግ ሁለት ጊዜ በቴሎቪዥን በፕሮግራም መልክ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡

የምክክርና ምርመራን ቀን በማስመልከት በተንቀሳቃሽ ስልክ አጭር መልዕክት ተላለፈ

የምክክርና ምርመራ አገልግሎት ቀን አከባበር “መመርመራችን ለቤተሰባችን ” በሚል መሪ ቃል በሞባይል መልዕክት ለ 1,000,000 ያህል ሰዎች በቀጥታ ተሰራጭቷል፡፡

 

በምክክርና ምርመራ አገልግሎት የተሰማሩ በጤና ተቋማት የሚገኙ ካውንስለሮች ኬዝ ኮንፈረንስ ለሶስት ቀናት የአቻ ለአቻ የልምድ ልውውጥና ኬዝ የተመረጠ ጠቃሚ የሆነ ርዕስ ላይ ትምህርታዊ ጥያቄና መልስ የተካሄደ ሲሆን በአገልግሎቱ ያጋጠማቸው ችግሮች በካውንሰለሮች ቀርቦ መልስ ተሰጥቶበታል፡፡

በወጣቶች የክረምት ንቅናቄ ላይ ብዙ ወጣቶች በፈቃደኝነት የኤች አይ ቪ ምርመራ አደረጉ

በከተማው የክረምት የወጣቶች ዘመቻ ላይ የኤች አይ ቪ/ኤድስ የመከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራሞ ከ20,000 በላይ ወጣቶች ንቅናቄ የተፈጠረ ሲሆን የምክክርና ምርመራ አገልግሎቶች ወጣቱ እንዲመረመሩ በተደረገው ጥረት መሰረት ብዙ ወጣቶች ምርመራ አድርገዋል፡፡

 

የአባላዘር በሽታን ለመከላከልና ለማከም የሚያስችሉ ክሊኒኮች ተከፈቱ

የአባላዘር በሽታዎችና ኤች አይ ቪ/ኤድስ በሚል ፕሮጀክት በይበልጥ የተጋለጡ ሴተኛ አዳሪዎች ከቤተሰብ መምሪና ከሶስት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሚስጠራዊነታቸው የተረጋገጠ ልዩ የሆኑ የህክምና ክሊኒኮች በአራዳና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች በመክፈት የምክክርና ምርመራ የአባላዘር በሽታዎች፣ ኮንዶም ትምህርትና ስርጭት፣ የአቻ ለአቻ ትምህርት ለ3,000 ሴተኛ አዳሪዎች እየተሰጠ ይገኛል፡፡