አጋርነት እና ትስስር
በተናጠል የሚከናወን እና ከኤች.አይ.ቪ እንዲሁም ከኤድስ ጋር ተያያዥነት ያለው ስራ የሚፈለገውን ውጤት ሊያስገኝ አልቻለም፡፡ የወረርሽኙ መጠን እና የሚያስከትለው ጉዳት በይበልጥ የተጠናከረ እና የተባበረ እንቅስቃሴ የሚያስፈልገው ነው፡፡ እስከአሁን ድረስ የሃብቶችን መደራረብ እና የስራ እንቅስቃሴዎችን ድግግሞሽ ለማስቀረት እንዲሁም ውጤታማ የሆነ እና ወጪ ቆጣቢ የሃብቶች አጠቃቀም ለማረጋገጥ የሚያስችል ዘዴ አልነበረም፡፡
ይህንን እውነታ በመረዳት የአዲስ አበባ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት እ.ኤ.አ. ከ2ዐዐ4 ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ ስር ለኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ የሚሰጡ ምላሾችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማቀናጀት የሚያስችል መድረክ ወይም ዘዴ ለመፍጠር ሞክሯል፡፡ ለዚህም ውጤት ይረዳ ዘንድ ባለድርሻዎች የንኡስ አጋርነት መድረኮችን ለመመስረት በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህም የትብብር መድረኮች የሚያተኩሩት በአይኢሲ/ቢሲሲ፣ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የምክር እና የምርመራ አገልግሎት፣ የእንክብካቤ እና ድጋፍ ወዘተ. ላይ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ በእድገት የአዲስ አበባ የኤድስ አክሽን ኔትዎርክ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
ይህ ኔትዎርክ እውን ከሆነ በኋላ 36 መስራች አባላት የአዲስ አበባ ከተማ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ከአክሽን ኤድ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የትብብር መድረክ ክፍሎችን በመዋቅሩ ውስጥ በመፍጠር ንኡሳን መድረኮች በይበልጥ ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲሰሩ የቴክኒክ ድጋፍ የመስጠት ስራ ሰርቷል፡፡
ሆኖም ግን ጽ/ቤቱ መሠረታዊ የአሰራር ለውጥ ንድፍ ካዘጋጀ በኋላ የመድረኩን የእለት ተእለት ስራዎች ለመምራት ሁለት ሙያተኞች የተቀፉበት የአጋርነት እና የትስስር ቡድን መስርቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ይህንን የጋርነት ሞዴል ከብሔራዊ የአጋርነት መድረክ ጋር ለማጣጣም በሁሉም ደረጃዎች ጠንካራ እንኳን ባይሆንም ልዩ ልዩ ንኡሳን መድረኮች እንዲፈጠሩ ተደርጓል፡፡
በአሁኑ ወቅት ያለውን የንኡሳን መድረኮች ትብብር ወይም አጋርነት የወቅቱን ሁኔታ ለመገምገም እንዲቻል ከነሐሴ 19 - 21/2ዐዐ1 ዓ.ም ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ ስለሆነም ኤኤንኦፒኤ እና የአዲስ አበባ የእድሮች ልማት የፀረ-ኤድስ አጋርነት ንኡሳን መድረኮች አንፃራዊ በሆነ መልኩ ተደራጅተው ፈቃድ ተሰጥቶአቸዋል፡፡ በእድሮች ረገድ መድረኩ የተመሰረተው ከከተማ እስከ ቀበሌ ባለው ደረጃ ነው፡፡
የመንግስት እና የሚዲያ ንኡሳን መድረኮች በሚገባ የተደራጁ አይደሉም፡፡ ስለሆነም ረጅም ርቀት መሄድ ያስፈልጋል፡፡ የመያዶች ንኡስ መድረክ ከመነሻው የተደራጀው ከላይ ከተጠቀሱት አሳሳቢ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ሂደቱም የእንክብካቤ እና የድጋፍ መድረክን የሚያጠናክር ነው፡፡ ይህም በመያድ ንኡስ መድረክ ደረጃ መሻሻል ይገባዋል፡፡ አላማውም ከብሔራዊ የጋርነት መድረክ ሞዴል ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡
የሃይማኖት ተቋማት በከተማ ወይም በክልል ደረጃ አልተደራጁም፡፡ በእርግጥ በብሔራዊ ሴክሬታሪያት ደረጃ የሚንቀሳቀስ እና ኢትዮጵያ ኢንተርፌዝ ዲቨሎፕመንት አሶሲየሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡ የወጣቶች እና የሴቶች ፌዴሬሽኖች ከከተማ እስከ ቀበሌ ደረጃ እንዲደራጁ ተደርጐ ከሚመለከታቸው አመራሮች ጋር የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ጥረት ተደርጓል፡፡ አላማውም በአሁኑ ወቅት ባሉት መዋቅሮች ውስጥ የፀረ-ኤድስ መድረኮችን እንዲያቋቁሙ ለማድረግ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ከሞላ ጐደል 41 የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ያሉ ቢሆንም የእነዚህ ማህበራት ሁሉም አደረጃጀቶች በፀረ-ኤችአይቪ እና ኤድስ የአጋርነት መድረክ በብሔራዊ ደረጃ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን በከተማ ደረጃ አልተደራጁም፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ከግምት ውስጥ በማስገባት የአዲስ አበባ ከተማ የኤችአይቪ እና ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ንኡሳን መድረኮችን አመሰራረት በማጠናቀቅ የክልል እና የክፍለ ከተማ የአጋርነት መድረኮችን ለመመስረት ይሻሉ፡፡













