የሀብት ማፈላለግና ማስተላለፍ
የሀብት ማፈላለግና ማስተላለፍ አንድ ራሱን የቻለ ቡድን ሲሆን፣ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ኃላፊነቱን ወስዷል፡-
- የኤችአይቪ/ኤድስ ፕሮግራሞችን ለመደገፍ ፈቃደኞች የሆኑ ምንጮችን በመለየት ግንኙነቶች መመስረት፣
- በከተማው ውስጥ በመስራት ላይ ላሉ ልዩ ልዩ የሚተገብሩ አጋሮች የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣
- በሃብቶች ማደራጀት ስትራቴጂ እና በገንዘብ አጠቃቀም ቴክኒኮች ረገድ ስልጠና መስጠት
- የሃብቶች ማፒንግ ትንተና ማካሄድ (በፕሮግራም እንዲሁም በሰው ሃይል፣ በማቴሪያል እና በፋይናንስ ክፍተቶች)
- የሃብት ማደራጀት ስትራቴጂ እና የክፍተት ትንተና ማጐልበት
- የሃብት ማደራጀት መድረኮች ማደራጀት
- የፕሮጀክት ግምገማ ማከናወን
- የሃብቶች ማደራጀት መመሪያ ማጐልበት እና/ወይም ተግባራዊ ማድረግ
- ገንዘብ ረጂ ኤጀንሲዎችን በመለየት ገንዘብ ለማሰባሰብ እንዲረጃ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ማዘጋጀት
- የፕሮጀክት አቅም ግምገማ ቼክሊስት ማዘጋጀት
- ለተግባሪ አጋሮች ማለትም አይፒ፣ ሲቢኦ እና ኤፍቢኦ የአቅም ግምገማ ማካሄድ
- ሃብቶችን በማሰራጨት የተመደቡትን ገንዘቦች መክፈል እንዲሁም ለሴክተር ቢሮዎች መመደብ፣ አይፒኤስ፣ ሲቢኦ እና ኤፍቢኦ
- የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት ለፀደቁ ፕሮጀክቶች የፋይናንስ ስምምነት ሰነዶች ማዘጋጀት
- የፕሮጀክት የሶስትዮሽ ስምምነት የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት
- የሀብት ማፈላለግና ማስተላለፍ ቡድን በየሩብ አመቱ ለጽ/ቤቱ የሚቀርብ የእቅድ ትግበራ ሪፖርት ማዘጋጀት
- የጽ/ቤቱን የሃብቶች መረጃ ዳታቤዝ መመስረት (በጠቅላላው የተላለፈ፣ የተደራጀ እና በከተማ ደረጃ የተሰራጨ መረጃ)
- በሃብቶች ማደራጀት ስትራቴጂ እና በፕሮጀክት ግምገማ ሂደት እንዲሁም ከሌሎች ክልሎች ጋር ስላለው የሥራ አፈፃፀም የልምድ ልውውጥ ማድረግ
- በሃብቶች አደረጃጀት ወይም አጠቃቀም እና በፕሮጀክት ስራ አመራር ረገድ በውጪ ሃገር እና በሃገር ውስጥ የአጭር ጊዜ ስልጠና መስጠት













