ማህበራዊ አደረጃጀት እና ሜንስትሪሚንግ

 

የህብረተሰቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመቅረፍ ስትራቴጂያዊ ተደርገው ከተወሰዱት አሰራሮች መካከል ማህበራዊ አደረጃጀት አንደኛው ነው፡፡

የዚህ እርምጃ ዋነኛው አላማ ሰዎች አኗኗራቸውን ለማሻሻል በሚደረጉት ጥረቶች ባለቤት እና መሪዎች እንዲሆኑ ለማድረግ ነው፡፡

ከማህበራዊ አደረጃጀት እንቅስቃሴዎች መካከል አንዱ የማህበረሰቡ ውይይት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በከተማዊቱ በሁሉም ቀበሌዎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ አላማውም ማህበረሰቦች በአካባቢ ደረጃ ቀጣይነት ያለው ውይይት በማድረግ ችግሮቻቸውን እንዲገልፁ እና በተጨባጭ ባጋጠሟቸው ችግሮች ዙሪያ መፍትሄዎች ለማግኘት እንዲችሉ ነው፡፡ ማህበረሰቦች በውይይቶች ላይ ተሳታፊ በመሆን ስለ ኤችአይቪ/ኤድስ በይበልጥ የሰረፀ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና እያንዳንዱን የህብረተሰቡን አባል የሚመለከቱ ችግሮችን በይበልጥ እንዲረዱ ማድረግ ነው፡፡

ከዚህም ባሻገር ይህ እንቅስቃሴ የአካባቢ ማህበረሰቦች የኤችአይቪ/ኤድስን ስርጭት ለማስቆም በማህበራዊ እና በግለሰብ ደረጃ አወንታዊ የባህርይ ለውጥ እንዲያመጡ የማድረግ አላማ ያለው ነው፡፡ ይህ ሂደት ወንዶች፣ ሴቶችና ወጣቶች፣ ከኤችአይቪ ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎች፣ ድሆች እና የተሻለ ገቢ ያላቸው ሃብታም ሰዎችን የሚያካትት ነው፡፡ እንቅስቃሴውም በይበልጥ ባህላዊ እና ማህበራዊ እሴቶችን በመጠቀም የማህበረሰቡ አባላት የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው እንዲፈቱ ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም ራስን በመግዛት፣ በእራስ ላይ እምነትን በማሳደር እና ቀጣይነት ያለው ለውጥ ይመጣ ዘንድ ከማህበረሰቡ የተቀናጀ ምላሽ በማግኘት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ከማህበረሰብ አደረጃጀት ፕሮግራሙ አንፃር አንድ ክፍል ተደርጐ የሚወሰደው ይህ የማህበረሰብ ውይይት በሚኒሊክ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የስብሰባ አዳራሽ፣ አዲስ አበባ ከኦክቶበት 27-28/1/1999 ዓ.ም በባለድርሻ አካላት በተካሄደ ስብሰባ ተገምግሟል፡፡ ይህም ስበሰባ በዚህ ውይይት አሰላጮች በቀረቡት ሪፖርቶች መሠረት የማህበረሰብ ውይይት ቡድኖች ያከናወኗቸውን ስራዎች በመገምገም ወደፊት ሊሻሻሉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች የውሳኔ ሃሳብ ሰጥቷል፡፡ የተለያዩ የማህበረሰብ ውይይት ቡድኖች የልምድ ልውውጥ በማድረግ የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ እንደ እድር፣ የሚዲያ ሰዎች፣ ከኤችአይቪ ጋር ነዋሪ የሆኑ ሰዎች እና ልዩ ልዩ አካላት ከማህበረሰቦች ጋር ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡

የበጐ ፈቃደኞች የፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች

እነዚህ ሰዎች ከማህበረሰቡ መካከል የሚመረጡ ሲሆኑ፣ ከቤት ለቤት በመዘዋወር የኤችአይቪ/ኤድስ ትምህርት ይሰጣሉ፡፡

በቀበሌዎች ደረጃ የሰለጠኑ 912 በጐ ፈቃደኞች አሉ፡፡

የት/ቤት የፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴዎች

በመጀመሪያ እና በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የአቻ እና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት ስለ ኤችአይቪ እና ኤድስ ግንዛቤ ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡

በቀድሞ የበጀት አመት የአቻ ለአቻ እና የሕይወት ክህሎቶች ስልጠና ለ651 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፣ ለ63 የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለአንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህራን እና ተማሪዎች ተሰጥቷል፡፡

ከት/ቤት ወጣት ተማሪዎች አንፃር የተከናወኑ የስራ እንቅስቃሴዎች

በክረምት ጊዜ ይህ መ/ቤት ከአዲስ አበባ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ልዩ ልዩ የሥራ እንቅስቃሴዎችን አከናውኗል፡፡ ከእነዚህም መካከል1-

  1. የክረምት የትምህርት ፕሮግራም ይገኙበታል፡፡ መደኛ ት/ቤቶች በሚዘጉበት ወቅት 68878 ተማሪዎች የሁለት ወራት የማጠናከሪያ ትምህርት የተሰጣቸው ሲሆን፣ ከእየእለቱ ትምህርት መካከል ኤችአይቪ/ኤድስ ዋነኛው ነበር፡፡

ይህ የክረምት ትምህርት ፕሮግራም በስነ-ተዋልዶ ጤና እና በኤችአይቪ/ኤድስ ትምህርት ላይ ያተኮረ ትምህርት ለመስጠት 156695 ወጣቶችን አንቀሳቅሷል፡፡

  1. በወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከተነደፉት ሌሎች የበጋ የፕሮግራም እንቅስቃሴዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ ለምሳሌ ልዩ ልዩ የስፖርት ውድድር፣ ደም መለገስ፣ የአካባቢ ፅዳት እንዲሁም ሌሎች እንቅስቃሴዎች 6ዐ54ዐ8 ወጣቶች በኤችአይቪ/ኤድስ ላይ ልዩ ልዩ መልእክቶች እንዲደርሷቸው ተደርጓል፡፡

የወጣቶች ውይይት

የወጣቶች ውይይት በአንድ ቀበሌ/ስፍራ የተካሄደ ሲሆን፣ ከ1ዐዐዐዐ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ይህ ውይይት ቀጣይ እና በወጣቶች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህም የውይይት እርስ በዋናነት ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር ተዛማጅነት ባላቸው ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የወጣት ማእከላትን ማጠናከር

የአዲስ አበባ የወጣቶች እና የስፖርት ቢሮ በርካታ የወጣቶች ማእከላትን በመመስረት ላይ ይገኛል፡፡ መ/ቤታችን ለ47 የወጣት ማእከላት የመሳሪያዎች ድጋፍ ሰጥቷል፡፡

እነዚህ የወጣት ማእከላት ወጣቶች ለመረጃ የተሻለ ተደራሽነት እንዲኖር በማድረግ ረገድ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ከዚህም ለላ ወጣቶች አንዳንድ የኤችአይቪ እና የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን እንዲያገኙ፣ በቤተመፅሐፍት ጊዜያቸውን በማሳለፍ፣ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች በመጫወት፣ ኮምፒውተሮችን እና ኢንተርኔቶችን በመጠቀም አመቺ በሆነ መልኩ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ለማድረግ ያስችላል፡፡

ከዚህም ሌላ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የወጣት ማእከላት መካከል አንዱን በመምረጥ መ/ቤታችን የኤድስ መረጃ ማእከልን መስርቷል፡፡

አመራር እና ሜንስትሪሚንግ

በከተማው አስተዳደር የሜንስትሪሚንግ ሕግ አውጥቷል፡፡ ከዚህም ውስጥ የትግበራ መመሪያዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ በሕጉ አማካኝነት የኤድስ ፈንድ አጠቃቀም መመሪያም ተዘጋጅቷል፡፡ ለዚህም አላማ የሆነው በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የሴክተር ሜንስትሪሚንግ በይበልጥ እንዲጠናከር ለማድረግ ነው፡፡

ከዚህም ሌላ የከተማው አስተዳደር በመስጠት ላይ ያለውን ጠንካራ አመራር ለመደገፍ በተለይም በከተማ እና በክፍለ ከተማ ደረጃዎች ለምክር ቤት አባላት ስልጠናዎች በመሰጠት ላይ ናቸው፡፡ የከተማው አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ልዩ ልዩ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር እንቅስቃሴዎችን በሚኖሩባቸው ቀበሌዎች ደረጃ እንዲፈትሹ ለማድረግ የሚያስችል ቼክሊስት ተዘጋጅቷል፡፡

በቅርቡ ለ12ዐ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፣ ከዚህም ጋር ተያይዞ ለ4ዐ2 የጉለሌ ክፍለ ከተማ የምክር ቤት አባላት ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡