ክፍለ ከተሞች
የአዲስ አበባ የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የተመሰረተው በፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ ረገድ የሚካሄዱትን እንቅስቃሴዎች ከልዩ ልዩ ሴክተሮች እና ከታችኛው የሕብረተሰብ ክፍል ጀምሮ ለማንቀሳቀስ ነው፡፡ በዚህም እንቅስቃሴው ወረርሽኙ በአዲስ አበባ እንዳይስፋፋ ጥረት ያደርጋል፡፡ የአዲስ አበባ ኤች.አይ.ቪ / ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በአስሩም ክፍለ ከተሞች ዴስኮች አሉት፡፡
ይህ ጽ/ቤት በክፍለ ከተማ ደረጃ ከሚገኙ የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዴስኮች እንዲሁም በቀበሌ ደረጃ ደግሞ ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሰራተኞች ጋር በሕብረት ይሰራል፡፡ የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ ዴስኮች በአካባቢዎቻቸው የሚከናወኑትን ስራዎች የሚያስተባብሩ ከመሆኑም ሌላ ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጋር ተያያዥ የሆኑ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ፍላጐት ካላቸው የአካባቢ ቡድኖች እና የማህበረሰብ አደረጃጀቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ይሰራል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የኤችአይቪ/ ኤድስ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ጽ/ቤት በከተማይቱ ያለውን የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ወረርሽኝ ከታችኛው የሕብረተሰብ ክፍል ጀምሮ ምላሽ ለመስጠት እና ለማበረታታት ከላይ ከተጠቀሱት ዴስኮች ጋር በሕብረት ይሰራል፡፡
በክፍለ ከተማ ደረጃ ያሉ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዴስኮች በአዲስ አበባ የኤች.አይ.ቪ / ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ስር የሚሰሩ ሲሆን፣ የሚመሩትም በክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ነው፡፡ እያንዳንዱ ክፍለ ከተማ በአብዛኛዎቹ የከተማው ክፍሎች ተፈፃሚነት ያላቸው የፀረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች አሏቸው፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች በእያንዳንዳቸው የክፍለ ከተማ አስተዳደሮች የሚፈፀሙ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ክፍለ ከተማ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክር ቤት ቁጥጥር ስር ያለ እና ከእርሱም አመራር የሚወስድ ነው፡፡ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክር ቤት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ቢያንስ 1ዐ አባላት ያሉት ሲሆን፣ እነዚህም ባለድርሻ አካላት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ማህበረሰባዊ ድርጅቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ክቡራን ግለሰቦች ወዘተ. ናቸው፡፡ በቀበሌም ደረጃ ተመሳሳይ መዋቅር አለ፡፡













